የሀገር ውስጥ ዜና

የኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች የምርት ዕድገት በሀገር ምርት ለመኩራት ወሳኝ ነው ተባለ

By ዮሐንስ ደርበው

June 22, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር ምርት የሚኮራ ትውልድ ለመፍጠር የኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች የምርት እድገት እና ጥራት ወሳኝ ነው ሲሉ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ተናገሩ፡፡

ለ12ኛ ጊዜ 481 ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች ወደ መካከለኛና ለመጀመሪ ጊዜ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር የምረቃና ሽግግር መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ የፋይናንስ አቅርቦት በማመቻቸት፣ የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎችን በማቅረብ፣ አጫጭር የሙያ ስልጠናዎች በመስጠት እና የካፒታል ሊዝ ፋይናንስ በማድረግ ስራ ፈጣሪዎችን እየደገፈ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሽግግር የሚያደርጉ ስራ ፈጣሪዎች እና ኢንተርፕራይዞች መንግስት ሁሉንም አይነት ድጋፍ ሊያደርግ እንደማይችል ሊገነዘቡ ይባል ብለዋል፡፡

በመሆኑም መለወጥ፣ ማደግ፣ መበልፀግ የሚቻለው የግል ጥረትን ማዕከል በማድረግ ሲሰራ ነው ማለታቸውን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሁሉም የዕድገት ተኮር ዘርፎች የተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

ለሁሉም ተሸጋጋሪ ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች እውቅናና ሽልማት የተከናወነ ሲሆን÷ በክፍለ ከተማና በወረዳ ከአንድ እስከ ሶስት ደረጃ የያዙ ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!