የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል ከ54 ቢሊየን ብር በላይ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኑ

By ዮሐንስ ደርበው

June 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ54 ቢሊየን 280 ሚሊየን 538 ሺህ ብር የተገነቡ 19 ሺህ 912 ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡

ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑት ፕሮጀክቶች ከ30 ሚሊየን በላይ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡

ቢሮው ዛሬ ባወጣው መግለጫ÷ ፕሮጀክቶቹ ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ብሏል፡፡

ለዚህም ሕብረተሰቡ ተገቢውን እንክብካቤ ሊያደርግ እንደሚገባ ቢሮው አሳስቧል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!