የሀገር ውስጥ ዜና

ከ275 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

By Meseret Awoke

June 24, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጉምሩክ ኮሚሽን ከሰኔ 9 እስከ 15 ባደረገው ክትትል ከ275 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽኅፈት ቤቶች መያዙን አስታወቋል፡፡

199 ሚሊየን የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና ከ75 ሚሊየን ብር በላይ የወጭ በድምሩ ከ275 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች ናቸው በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የተያዙት፡፡

በቁጥጥር ሥር ከዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሐኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች የጦር መሣሪያዎች ፣ የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች እና የመሣሰሉት ይገኙበታል ተብሏል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የጉምሩክ ኮሚሽን ሠራተኞች ፣ የፌደራል ፖሊስ ፣ የክልል ፖሊስ አባላትና ኅብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ ፣ በበረራና በጥቆማ መያዛቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ 16 ግለሰቦችና 12 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተመልክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!