ስፓርት

39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር እየተካሄደ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

June 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር መካሄድ ጀምሯል፡፡

ውድድሩ እየተካሄደ የሚገኘው በአዲስ አበበባ ሲሆን÷ መነሻ እና መድረሻውን ሰሚት ማድረጉም ተገልጿል፡፡

በውድድሩ÷ 12 ክለቦች፣ 2 ክልሎችና 1 ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 354 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ እየተሳተፉ ነው፡፡

ለውድድሩ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ መዘጋጀቱን እና ከ1ኛ እስከ 8ኛ ለሚወጡ አትሌቶች ሽልማት እንደሚበረከት ተመላክቷል፡፡፡

38ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር ባለፈው ዓመት በባሕር ዳር ከተማ መካሄዱ ይታወሳል፡፡