የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የ2ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

By Mikias Ayele

June 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የሁለተኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ሁለተኛውን ዙር የአንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ከተማ አስጀምረዋል፡፡

በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተሞች ክላስተር አስተባባሪ  መስፍን መላኩ በተገኙበት በጅማ ዞን ኦሞ ናዳ ወረዳ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

በክልሉ በዘንድሮው ክረምት ከ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን የሚበልጡ የተለያዩ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አስታውሶ ኦ ቢ ኤን ዘግቧል፡፡

በሙክታር ጣሃ