የሀገር ውስጥ ዜና

የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰመራ ከተማ ተከበረ

By Melaku Gedif

June 28, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 444ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተከብሯል፡፡

በዓሉ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ነው የተከበረው፡፡

በአከባበር ስነ-ስርዓቱ ሰላት እና ተክቢራን ጨምሮ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ተከናውነዋል፡፡