የሀገር ውስጥ ዜና

የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በድሬዳዋ ከተማ ተከበረ

By Melaku Gedif

June 28, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 444ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በድሬዳዋ ከተማ ተከብሯል፡፡

በዓሉ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተገኙበት በሰላት እና ተክቢራን እንዲሁም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ተከብሯል፡፡

በአከባበር ስነ-ስርዓቱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የድሬዳዋ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አመራሮች ተሳትፈዋል።