የሀገር ውስጥ ዜና

የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሐረር ከተማ ተከበረ

By Melaku Gedif

June 28, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 444ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሐረር ከተማ ተከብሯል፡፡

በዓሉ በርካታ የእስልምና እምነትተከታዮች በተገኙበት ሰላት እና ተክቢራን ጨምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ነው የተከበረው፡፡

በሐረር ከተማ በተካሄደው የሰላት ስነ-ስርዓት ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝበ ሙስሊም ተገኝቷል፡፡

የሐረር ጁምዐ መስጅድ ኢማም ሼክ ሙክታር ሙባሪክ ÷ በዓሉ የመስዋዕትነትና የመታዘዝ በመሆኑ ለፈጣሪ መገዛት እንደሚያስፈልግ እና ለሠላምና አንድነት ህዝበ ሙስሊሙ መትጋት እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብርም በመተጋገዝና በመደጋገፍ ሊሆን እንደሚገባ ሼክ ሙክታር አሳስበዋል።

በተሾመ ኃይሉና ቱጂ አብዲ