የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ጌታቸው ረዳ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ የመተጋገዝ ባህሉን ይበልጥ እንዲያጠናክር አስገነዘቡ

By Alemayehu Geremew

June 28, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ ያለውን የመተጋገዝ ባህል ይበልጥ እንዲያጠናከር ጠይቀዋል፡፡

1ሺህ 444ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በመቀሌ ከተማ መከበሩን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አቶ ጌታቸው ረዳ በበዓሉ አከባበር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ በአካባቢያችን ያሉት ተፈናቃይ ወገኖችን ለማገዝ እያደረጋችሁ ያለው በጎ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

የትግራይ ክልል ከፍተኛ ምክርት ቤት ኃላፊ ሓጂ አደም አብዱልቃድር በበኩላቸው÷ በተፈጠረው ሰላም በዓሉን ተረጋግተን ማክበር ችለናል ነው ያሉት፡፡

#Ethiopia