አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ“ቲታን” ሰርጓጅ ጀልባ ከፊል ስብርባሪ በዛሬው ዕለት መገኘቱ ተገለጸ፡፡
የአሜሪካ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች የጀልባዋ የፊት እና የኋላ ክፍል ስብርባሪዎች መገኘቱን ተናግረዋል።
በዚህም ካናዳ ሴንት ጆንስ በተባለው አካባቢ ሆራይዘን አርክቲክ ከተሰኘችው መርከብ ላይ የሰርጓጅ ጀልባዋ ከፊል ስብርባሪ አካል መውረዱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
“ቲታን” የተሰኘችው ሰርጓጅ መርከብ ታይታኒክን ለመጎብኘት ያሰቡ አምስት ጎብኚዎችን ይዛ ወደ ሥፍራው በማቅናት ላይ ሳለች ደብዛዋ መጥፋቱ ይታወሳል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!