የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ብቁ የሰው ኃይል ለመፍጠር በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገለጹ

By ዮሐንስ ደርበው

June 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር ብቁ የሰው ኃይል፣ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ፡፡

የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የምርታማነት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡

የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሚኒስቴሩ ብቁ የሰው ኃይል፣ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ እየሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ለዚህ ተግባር መሳካትም መገናኛ ብዙኃን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

በሀገሪቱ 1 ሺህ 800 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መኖራቸውን ጠቁመው÷ ይሁን እንጂ በሕብረተሰቡ ዘንድ የለውጥ ተቋማት አድርጎ በመረዳት ረገድ ውስንነት አለ ነው ያሉት፡፡

ሀገራት የበለጸጉት በሙያ ተቋማት በሚገኙ አዳዲስ ግኝቶች በመሆኑ÷ የክኅሎት ልማት፣ የተቋማት አደረጃጀትና አዳዲስ የሙያ መስኮችን መክፈት ትኩረት እንደተሰጣቸው አረጋግጠዋል፡፡

በዘላለም ገበየሁ