የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በብሩንዲ የነጻነት ቀን በዓል ላይ ተካፈሉ

By Mikias Ayele

July 01, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የብሩንዲ 61ኛ ብሔራዊ የነጻነት ቀን በዓል ላይ ተሳትፈዋል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የብሩንዲ ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የነጻነት ቀን በዓሉን አስመልክቶ ለብሩንዲ ሕዝብ እና መንግስት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዓሉ በወታደራዊ ትርኢት እና በተለያዩ ስነ ስርዓቶች መከበሩን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ብሩንዲ ከቤልጂየም ቅኝ ግዛት ነጻ የወጣችው ከ62 ዓመታት በፊት በዛሬው ዕለት ነበር።

የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ለብሩንዲ የነጻነት ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።