የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የ2015 የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ

By Alemayehu Geremew

July 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል የ2015 የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በምሥራቅ ሸዋ ዞን ተካሄደ።

ከክልል እስከ ወረዳ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና ከክልሉ የተወጣጡ ግንባር ቀደም ወጣቶች በመርሐ- ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በዕለቱም የችግኝ ተካለ፣ የቤት ዕድሳት እና የደም ልገሳ መከናወኑን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በ2015 የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 9 ነጥብ 5 ሚሊየን ወጣቶች እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡

በዚህም ከ23 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ነው የታሰበው፡፡

በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱም 3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የሚገመት አገልግሎትእንደሚሰጥ ነው የተመላከተው፡፡