የሀገር ውስጥ ዜና

በቢሾፍቱ ከተማ በ2 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

By ዮሐንስ ደርበው

July 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ ከተማ በ2 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነቡ 85 ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡

በዛሬው ዕለት ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል÷ ደረጃውን የጠበቀ የአስፋልት መንገድ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣  እንዲሁም የገበያ ማዕከል እና የሕዝብ ቤተ መጻሕፍትን ጨምሮ ሌሎችም እንደሚገኙበት የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ፈቃዱ ተሰማ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የማንጨርሳቸውን ፕሮጀክቶች አንጀምርም፤ የጀመርነውን ደግሞ በጥራት ጨርሰን ለሕዝብ ተጠቃሚነት እናውላለን ብለዋል፡፡

በተመሳሰይ በኦሮሚያ ክልል በቦረና እና ባሌ ዞኖች እንዲሁም በነቀምት እና አሰላ ከተሞች የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት ሆነዋል፡፡