የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

By Melaku Gedif

July 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 13ኛው የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች ኮንፈረንስ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ እና ሌሎች አመራሮችን ጨምሮ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች የተውጣጡ ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡

አቶ ፍቃዱ ÷ ወጣቶች ለሀገር ሰላም እና አንድነት የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ እንደሆነ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡