የሀገር ውስጥ ዜና

አትሌት ገንዘቤ በአንትሪም ኮስት ግማሽ ማራቶን እንደምትሳተፍ  አስታወቀች

By Mikias Ayele

July 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በሰሜናዊ አየርላንድ አንትሪም ኮስት በሚካሄደው ግማሽ ማራቶን እንደምትሳተፍ አረጋግጣለች፡፡

አትሌት ገንዘቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጿ ባሰፈረችው መልዕክት÷ ነሐሴ 27 በሚካሄደው የአንትሪም ኮስት ማራቶን እንደምሳተፍ ስገልፅ በከፍተኛ ደስታ ነው ብላለች፡፡

ከዚህ በፊት በአየርላንድ አንተሪም ኮስት ተሳትፋ እንደማታውቅም ነው የገለጸችው፡፡

አድናቂዎቿ በተጠቀሰው ቀን እና ቦታ ተገኝተው እንዲያበረታቷትም ጠይቃለች፡፡