አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ፋህድ ኦባይድላህ አል-ሁመይድኒን (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው አምባሳደር ተሾመ የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም እያከናወናቸው የሚገኙ ፕሮግራሞችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪም አስካሁን የተከናወኑ የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ላይ ለአምባሳደሩ ገለጻ ማድረጋቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡