የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በፓሪስ ዓለም አቀፍ የፋሽን ንግድ አውደ ርዕይ ምርቶቿን እያስተዋወቀች ነው

By Amele Demsew

July 04, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ‘ቴክስ ዎርልድ ኢቮሉሽን ፓሪስ’ በሚል ስያሜ እየተካሄደ በሚገኘው የፓሪስ ዓለም አቀፍ የፋሽን ንግድ አውደ ርዕይ ላይ ምርቶቿን እያስተዋወቀች ነው፡፡

በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ማህሌት ኃይሉ እንደገለጹት÷ አውደ ርዕዩ በፋሽን ኢንዱስትሪው ያሉ አቅራቢዎችን እና ከገዢዎች የሚያገናኝ ነው፡፡

በአውደ ርዕዩ በሽመና እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተመረቱ የጨርቃ ጨርቅ ምርቶች፣ የቆዳ እና የቆዳ ውጤቶች እና የፈጠራ ፋሽን ስራዎች ቀርበዋል፡፡

ከ130 ሀገራት የተወጣጡ 29 ሺህ ዓለም አቀፍ ገዢዎች መሳተፋቸውን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአውደ ርዕዩ የኢትዮጵያን ምርቶች ለማስተዋወቅ እና አዳዲስ ገዢዎች ለመሳብ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተመላክቷል።