ስፓርት

ማሰን ማውንት ማንቼስተር ዩናይትድን ተቀላቀለ

By ዮሐንስ ደርበው

July 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን አማካይ ማሰን ማውንትን በይፋ አስፈርሟል፡፡

የላንክሻየሩ ክለብ ማሰን ማውንትን በአምስት ዓመት ኮንትራት ነው ያስፈረመው፡፡

ለአማካዩ ዝውውር 60 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ መደረጉን ጠቅሶ ቢ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

ማውንት በቼልሲ ቆይታው 195 ጊዜ ተሰልፎ 33 ጎሎችን ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡