የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል ሕዝባዊ ንቅናቄ ተጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

July 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል ሕዝባዊ ንቅናቄ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ተጀመረ፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ ንቅናቄውን አስጀምረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ የትምህርትቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል አስጀምሯል፡፡

በሕዝባዊ ንቅናቄው የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሃብቶች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች መገኘታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ማሻሻል ሀገር አቀፍ ሕዝባዊ ንቅናቄ በአዲስ አበባ ማስጀመሩ ይታወሳል።