አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ912 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 2 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት ቫይረሱ የተገኘባቸው የ20 እና 25 አመት ወጣት ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ከዚህ ውስጥ አንደኛው ከፑንትላንድ የተመለሰና በጅግጅጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፥ ሌላኛው ደግሞ ከኬንያ የተመለሰና በሞያሌ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኝ መሆኑ ተገልጿል።
አሁን ላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 133 የደረሰ ሲሆን፥ 66 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል ነው የተባለው።
ከዚህ ውስጥ 7 ሰዎች አዲስ ያገገሙ መሆናቸውም ነው የተገለጸው።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።