አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሱዳኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ኤልሳዲግ አሊ እና ከኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱልጣን ቢን ሳድ አል-ሙራይኪ ጋር ተወይይተዋል፡፡
አምባሳደር ምስጋኑ በአዘርባጃን ባኩ ከተማ እየተካሄደ ካለው የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ (ናም) የሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ለጎን ነው ከከፍተኛ አመራሮቹ ጋር የተወያዩት፡፡
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ አምባሳደር ምስጋኑ ከቬትናም ም/የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ ሃንግ ቬት፣ ከማልዲቭስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አህመድ ካሌል እና ከጋምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቋሚ ፀሐፊ ሃቢብ ጃራ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡