የሀገር ውስጥ ዜና

ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

July 06, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) እና የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ መክረዋል።

ሁለቱ ተቋማት በሱዳን ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ያላቸው ቁርጠኝነት የማይናወጥ መሆኑን ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ኢጋድ እና የአፍሪካ ህብረት በሱዳን ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ፣ ጦርነቱ እንዲቆም እና ሀገሪቱን ወደ ፖለቲካው መስመር ለመመለስ በጋራ ጥረት እያደረጉ መሆኑንም አንስተዋል፡፡