አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የአስፈጻሚ ተቋማት የ2015 በጀት ዓመት የስራ ክንውን ግምገማ ተጀምሯል፡፡
የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚ ተቋማት÷ በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና በአስተዳደር ዘርፍ በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት በዝርዝር እንደሚገመግሙ ተመልክቷል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) እንደገለጹት÷ በዕቅድ ዘመኑ በክልሉ የተሻሉ አፈጻጸሞች ተከናውነዋል፡፡
ያልተከናወኑ ተግባራትን በቀጣዩ ዘመን የዕቅድ አካል በማድረግ ወደ ተግባር እንደሚገባም አረጋግጠዋል፡፡
ዛሬ የተጀመረው ግምገማ መልካም ተሞክሮዎችን ለማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም በቀጣዩ ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ያለመ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡