አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት ለ8 ሺህ 459 ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን የሐረሪ ክልል የኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ገለፀ።
ለ9 ሺህ 695 ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እንደነበር ተገልጿል፡፡
ከተፈጠረው 8 ሺህ 459 የሥራ ዕድል መካከል÷ በከተማ ለ5 ሺህ 199 እና በገጠር ወረዳ ለሚገኙ 3ሺህ 269 ወጣቶች መሆኑ ተመልክቷል፡፡
የተፈጠሩት የሥራ ዘርፎቹም÷ በከተማ ግብርና፣ በኢንዱስትሪና በተለያዩ አገልግሎት ዘርፎች መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ቢሮው በበጀት ዓመቱ በመንግሥትና በግል ተቋማት መካከል ከ88 ሚሊየን ብር በላይ የገበያ ትስስር መፍጠሩ ተገልጿል፡፡
በበጀት ዓመቱ ለኢንተርፕራይዞች ከ26 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የብድር አገልግሎት መሰጠቱም ነው የቢሮው ኃላፊ ሰሚራ ዩሱፍ ተናግረዋል፡፡