የሀገር ውስጥ ዜና

በአዳማ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

By Amele Demsew

July 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 111 ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ዛሬ ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል÷ የኦሮሚያ ልማት ማኅበር (ኦልማ) ሕንጻ፣ የአዳማ ከተማ ዘመናዊ መናኸሪያ እና የኢፈ ቦሩ ትምህርት ቤት ይገኙበታል፡፡