አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ2015 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለጤና መስክ ተማሪዎች መስጠት ጀምሯል።
የመውጫ ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ በቀጥታ በበይነ መረብ ከማዕከል እየተሰጠ ሲሆን ÷የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱረህማን ከድር( ዶ/ር ) በፈተና ጣቢያዎች በመገኘት ፈተናውን አስጀምረዋል፡፡
ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ከግል ኮሌጆች እና ከጤና ሚኒስቴር የተመደቡ በጠዋቱ ፈረቃ 304 ፣ ከሰዓት በኋላ 277 በአጠቃላይ 581ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡
ተፈታኞቹ የጠዋቱን ፈተና ያለምንም ችግር በጥሩ የፈተና ድባብ በማገባደድ ላይ እንደሚገኙም ነው የተገለጸው፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለ 1ሺህ 939 መደበኛ እና የማታ ተማሪዎቹ እንዲሁም 850 በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን የግል ትምህርት ተቋም ተማሪዎችን ጨምሮ በጠቅላላ 2 ሺህ 789 ተማሪዎችን የመውጫ ፈተና እንደሚያስፈትን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡