አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ሱዳን ሊሻገር የነበረ አደንዛዥ ዕፅ፣ የዝሆን ጥርስ፣ ደረቅ ጫት እና ነዳጅ በሑመራ ከተማ፣ ዲማ ፣ ባዕከር እና ራዊያን ኬላ ተያዘ፡፡
መነሻውን ሻሸመኔ ያደረገ እና ወደ ሱዳን ሊሻገር የነበረ 22 ማዳበሪያ ሐሽሽ እንዲሁም መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገ በቁጥር 25 ፍሬ ኮኬይን አደንዛዥ ዕፅ መያዙን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም ባለ 25 እና 20 ሊትር 42 ጀሪካን ነዳጅ ፣ 19 ካርቶን ደረቅ ጫት እንዲሁም አራት የዝሆን ጥርስ ተመያዙ ተገልጿል፡፡