አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ሞኒክ ሳንዛባጋንዋ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ሞኒክ ሳንዛባጋንዋ (ዶ/ር) አሁን ላይ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እየተካሄደ ስላለው ማሻሻያ ዙሪያ ለአቶ ደመቀ ገላጸ አድርገዋል፡፡
አቶ ደመቀ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
ኮሚሽኑ ለሚያካሂደው የማሻሻያ ስራ ኢትዮጵያ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ እንደሆነች መናገራቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡