የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የኑሮ ውድነትን ለማስተካከል የተጀመሩ ሥራዎች እንዲጠናከሩ የምክር ቤት አባላት አሳሰቡ

By Alemayehu Geremew

July 08, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከአገልግሎት አሰጣጥና ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስተካከል ከተማ አስተዳደሩ የጀመራቸውን ሥራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል የምክር ቤት አባላት አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ2ኛ ዓመት በ4ኛ መደበኛ ጉባዔው የከተማ አስተዳደሩን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ከአገልግሎት አሰጣጡና ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስተካከል ከተማ አስተዳደሩ የጀመራቸውን ሥራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል የምክር ቤት አባላት አሳስበዋል፡፡

የከተማዋን ሠላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ ሕዝቡን ያሳተፉ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አባላቱ ማስገንዘባቸውን የከንቲባ ጽኅፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ÷ የከተማ አስተዳደሩ የሕዝቡን የኑሮ ጫና የሚያቀሉ እና የኑሮ ውድነቱን መቋቋም ለሚያስችሉ ሥራዎች የተለየ ትኩረት ሰጥቶ በቀጣዩ በጀት ዓመት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡