የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት የሱዳንን ግጭት ለመፍታት ተቋቋመው የአራትዮሽ የመሪዎች ጉባኤ ተካሄደ

By Feven Bishaw

July 10, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት የሱዳንን ግጭት ለመፍታት ተቋቋመው የአራትዮሽ የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) የሱዳንን ግጭት ለመፍታት ያቋቋመውን የአራትዮሽ የመሪዎች ጉባኤን ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ ማስተናገዳቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህ ውይይት የሚሳተፉ የተለያዩ አገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

ከመሪዎቹ መካከልም የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የጅቡቲው የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር መሀመድ አሊ የሚገኙበት ሲሆን÷ በዛሬው ዕለትም መሪዎቹ በጉባኤው ተሳፈዋል፡፡