የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ ከተፈቀደላቸው ቀን ውጭ ሲያሽከረክሩ በተገኙ 1 ሺህ 351 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ

By Tibebu Kebede

May 02, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 351 አሽከርካሪዎች ከተፈቀደላቸው ተራ ቀን ውጭ ሲያሽከረክሩ በመገኘታቸው አስፈላጊው እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ለማስፈፀም የወጣውን የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃፀም መመሪያ ተከትሎ በተደረገ ቁጥጥር ከተፈቀደላቸው ቀን ውጭ ሲንቀሳቀሱ በተገኙ ኮድ 2 አሸከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን በኮሚሽኑ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የቀጠና ኃላፊ ኮማንደር በኃይሉ ደጀኔ ተናግረዋል።