አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተያዘው ዓመት 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን አስታወቁ።
የባለፈውን ዓመት ስኬት መነሻ በማድረቅ እቅዱ መዘጋጀቱን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ ኮቪድ19 ሥርጭትን ለመግታት እየተጋን፣ እንደ ሀገር አረንጓዴ ዐሻራ ማሳረፋችንን እንቀጥላለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በባለፈው ዓመት የክረምት ወቅት በኢትዮጵያ 4 ቢሊየን ችግኝ መተከሉ የሚታወስ ነው።
ከዚህ ባለፈ በአንድ ቀን 350 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያ የአለም ክብረወሰንን መስበሯ አይዘነጋም።