የሀገር ውስጥ ዜና

የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዓመታዊ ክብረ በዓል እየተካሄደ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

July 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዓመታዊ ክብረ በዓል እና የእውቅና ሥነሥርዓት በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በበዓሉ አከባበር ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰን ጨምሮ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮችና መኮንኖች ተገኝተዋል፡፡

“ምንጊዜም ለመዘመን እና ለድል አድራጊነት እንዘጋጅ” በሚል መሪ ሐሳብ ነው በዓሉ እየተከበረ የሚገኘው፡፡

የበዓሉ አከባበር ለሕግ የበላይነት መከበር የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የሠራዊት አባላት መዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡

በአከባበሩ ላይ የዕዙን ሁለንተናዊ ገጽታ የሚያንጸባርቁ የተለያዩ ሁነቶች እንደሚስተናገዱ ይጠበቃል፡፡

በሙክታር ጠሃ