አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት የልዑካን ቡድን በፖርቹጋል የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው ።
የጉብኝቱ ዋና አላማ የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ማጠናከር እና ፓርቹጋል በኢትዮጵያ ያላት የኢንቨስትመንት ፍስት እንዲጨምር ከተለያዩ የሚመለከታቸው የሀገሪቷ የዘርፉ አካላት ጋር መምከር መሆኑ ተገልጿል::
ቡድኑ በቆይታው ከፖርቹጋል የዓለም አቀፍ ንግድ እና የውጭ ኢንቨስትመንት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ዶቶር ቤርናርዶ ኢቮ ክሩዝ እና ከሀገሪቱ የኢንቨስትመንት እና ንግድ ፕሮሞሽን ተቋማት እንዲሁም የነፃ የንግድ ቀጠና ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።
ሁለቱ አካላት በተለያዩ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ስትራቴጂዎች ላይም መምከሩን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የልዑካን ቡድኑ የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዕድል ፣አማራጮች ላይ እና በመንግስት በተደረጉ የፖሊሲ ማሻሻዎች ላይ ለሀላፊዎቹ ገለፃ አድርገዋል።