አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የተመራ የፌዴራል መንግስት ልዑክ በአማራ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ ከክልሉ መንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡
በውይይት መድረኩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ መንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትርዴኤታ ካሳሁን ጎፌበማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት÷ የአማራ ክልል ሰላምና የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም የፌዴራል መንግስት የድጋፍ ቡድን በቀጣይ በሚኖሩት የልማት ስራዎች ድጋፍና ክትትል ዙሪያ ምክክር መደረጉን አንስተዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው በክልሉ የፊታችን ሐምሌ 10 ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐግብር በቂ ዝግጅት መደረጉን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡