የሀገር ውስጥ ዜና

በሶማሌ ክልል በአንድ ጀንበር 5 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት ተጠናቀቀ

By Alemayehu Geremew

July 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በአንድ ጀንበር 5 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ አብዱልቃድር ረሺድ እንደገለጹት÷ 1 ሚሊየኑ በጅግጅጋ ከተማ ይተከላል፡፡

ቀሪው 4 ሚሊየን በክልሉ በተለያዩ ዞኖች ይተከላል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ችግኞቹ የአየር ፀባይን መቋቋም የሚችሉ እንዲሁም ለምግብነት የሚውሉ መሆናቸውንም ነው ያመላከቱት፡፡

የፊታችን ሰኞ በሚከናወነው መርሐ ግብር ላይ የክልሉ ሕዝብ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡