አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል “ሂማሊያን ካታራክት ፕሮጀክት” ከተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የአይን ሕክምና ፕሮጀክቶች አስተባባሪ አቶ ሰማልኝ አቦ ÷ ለአንድ ሳምንት በሚካሄደው ነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና ከ700 በላይ ታካሚዎች አገልግሎቱን እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡
ከተለያዩ ወረዳዎች በልየታ ከመጡ ታካሚዎች በተጨማሪ በተለያየ መንገድ መረጃው ደርሷቸው ለሚመጡ ታካሚዎችም አገልግሎቱ እንደሚሰጥም ጠቁመዋል፡፡
የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና አገልግሎቱ ከሐምሌ 3 ቀን2015 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት የጀመረ ሲሆን÷ ለአንድ ሳምንት ይቆያል መባሉን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡