የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ እና ግብጽ ግንኙነት ላይ በጋራ የተሰጠ መግለጫ

By Meseret Awoke

July 13, 2023

ዛሬ ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም የአረብ ሪፐብሊክ ግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ተቀብለው አነጋግረዋል።

መሪዎቹ ባደረጉት ምክክር የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች የጋራ ጥቅም ባስጠበቀና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የባህል የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሻሻል ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ይህ የመሪዎቹ ቁርጠኝነት በቀጠናው ሰላምና ደህንነትን ለማስፈንና መረጋጋትን ለማስጠበቅ ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ባሻገር ሃገራቱ የሚያጋጥሟቸውን የጋራ ፈተናዎች ለመሻገርም ያስችላል።

ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ምክክር እልባት ያላገኘውን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተም በተከታዮቹ ሁለት ነጥቦች ላይ ተስማምተዋል፤

1) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትን እና የአሰራር ደንቦችን በተመለከተ በግብፅ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የሚካሄደውን ንግግር በፍጥነት ለማስጀመር እንዲሁም ንግግሩን በአራት ወራት ውስጥ አጠናቆ ከመግባባት ላይ ለመድረስ አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርጉ ተስማምተዋል።

2) ንግግሩ በሚካሄድበት ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ በ2015-2016 ዓ.ም የግድቡ የውሃ ሙሌት ወቅት ግብፅና ሱዳን ከወንዙ በሚያገኙት የውሃ አቅርቦት ላይ የጎላ ችግር እንዳያጋጥም ለማድረግ ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች።

//