የሀገር ውስጥ ዜና

እስከ ታሕሳስ ወር 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደተሃድሶ ማዕከላት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

By Melaku Gedif

July 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እስከ ቀጣዩ ዓመት ታሕሳስ ወር ድረስ 75 ሺህ የሚደርሱ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደተሃድሶ ማዕከላት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራን አስመልክቶ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር እየመከረ ነው፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሻንቆ ደለለኝ÷ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ በስኬት እንዲጠናቀቅ የአጋር አካላት ድጋፍ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ኮሚሽኑ እስከ ቀጣዩ ዓመት ታሕሳስ ወር መጨረሻ ድረስ 50 ሺህ የሚሆኑ ተዋጊዎችን ከትግራይ ክልል እና ቀሪ 25 ሺህ ደግሞ ከሌሎች ክልሎች ወደማዕከላቱ ለማስገባት መታቀዱን አንስተዋል፡፡

የሚሰናበቱ የቀድሞ ተዋጊዎችን ከማህበረሰቡ ጋር በዘላቂነት እንዲቀላቀሉ እና በልማት፣ በሰላምና በዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ እንዲሳተፉ እንዲሁም በዘላቂነት ወደ ሰላማዊ ኑሮ እንዲመለሱ የኢፌዴሪ ብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን የሚሰራ መሆኑ ይታወቃል።

በአሸናፊ ሽብሩ፣በዘመን በየነ እና ብርሃን ደሳለኝ