የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል ዘመቻ ተጀምሯል

By Shambel Mihret

July 17, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) በአማራ ክልል በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ተጀምሯል፡፡

ዘመቻው ከጥዋቱ 12 ሠዓት ጀምሮ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የተጀመረ ሲሆን ቀኑን ሙሉ የሚቀጥል ነው ተብሏ።

እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ በሚቆየው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር 260 ሚሊየን የችግኝ መትከያ ጉድጓድ እንደተዘጋጀም ተጠቅሷል፡፡

26 ሺህ ሄክታር መሬት በችግኝ እንደሚሸፈን እና በዕለቱም 5 ሚሊየን ሕዝብ በችግኝ ተከላው እንደሚሳተፍ ተጠቁሟል፡፡

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብሩ እንደየአካባቢው ሥነ-ምኅዳራዊ ሁኔታ እስከ መስከረም 2016 ዓ.ም ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን የአማራ ክልል በጠቅላላው 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል እቅድ ይዞ እየሠራ ይገኛል።

ኢትዮጵያ በሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 25 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል አቅዳ እየሠራች ትገኛለች።

በክልሉ በአንድ ጀምበር 260 ሚሊየን ችግኝ እንደሚተካ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡