አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዲፕሎማቶች በተዘጋጀላቸው ስፍራ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተገኝተው አሻራቸውን አኑረዋል።
በተጨማሪም መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።
የአለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች እና ሰራተኞችም በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞች ተከላ መርሃ ግብር ላይ ተሳትፈዋል።