የሀገር ውስጥ ዜና

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊት አረንጓዴ ዐሻራና ልማቱ ላይ የላቀ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገለጹ

By ዮሐንስ ደርበው

July 17, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአገር ሉዓላዊነትና ደኅንነት ከማስጠበቅ ባሻገር አረንጓዴ ዐሻራና ልማቱ ላይ የላቀ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።

የመከላከያ ሰራዊት አባላትና መኮንኖች በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ-ግብር አረንጓዴ ዐሻራቸውን ጦር ሃይሎች በሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ግቢ አኑረዋል።

ሰራዊቱ የሀገርን ሰላምና ደኅንነት ከማስበጠቅ ባለፈ በልማቱ ላይም ትርጉም ያለው ዐሻራ እያሳረፈ መሆኑን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመርሐ ግብሩ ላይ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተለይም በአረንጓዴ ዐሻራ መስክ የተቀመጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት ሰራዊቱ ባለፉት ዓመታት ችግኝ ሲተክል እና ሲንከባከብ መቆየቱን አስገንዝበዋል፡፡

ይህንንም ሚናውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያረጋገጡት፡፡