አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት እየተካሄደ በሚገኘው በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ከማለዳ ጀምሮ እስከ 8 ሰዓት ተኩል ድረስ 372 ሚሊየን በላይ ችግኝ መተከሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።
ከችግኝ ተከላ ሁነቶች መከታተያ ክፍል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት÷ በመላ ሀገሪቱ 500 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀንበር የመትከል መርሐ ግብር እንደቀጠለ ነው፡፡
በእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ክፍል 12 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ተኩል ድረስም ከ372 ሚሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል።
በመርሐ ግብሩ ህፃናት፣ ወጣቶች እና አረጋውያንን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ችግኝ በመትከል ታሪክ እየሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በምንተስኖት ሙሉጌታ