የሀገር ውስጥ ዜና

የክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

By Shambel Mihret

July 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 2ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔውን በታርጫ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባዔ አቶ ወንድሙ ኩርታ÷ምክር ቤቱ ባለፈው በጀት ዓመት በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ በሕገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሠረት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሲወጣ መቆየቱንም ጠቅሰዋል፡፡

ለታችኛው መዋቅር ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ከማድረግ አንጻር በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በታችኛው መዋቅር የሚታዩ ክፍተቶችን ከስሩ ለመፍታት የምክር ቤት አባላት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩም አሳስበዋል፡፡