የሀገር ውስጥ ዜና

118 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Melaku Gedif

July 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 118 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት መካከል 38ቱ ወደ የመን ለመግባት በሚያደርጉት ጥረት በህገ ወጥ ደላላዎች እጅ ወድቀው እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

80 የሚሆኑት ደግሞ በጅቡቲ የተለያዩ አካባቢዎች ስደት ላይ የነበሩ መሆናቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡