ዓለምአቀፋዊ ዜና

ኢራቅ ለኢራን የኤሌክትሪክ ክፍያ እንድትፈፅም የሚያስችል የስምምነት ህግ አሜሪካ አፀደቀች

By Mikias Ayele

July 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራቅ ለኢራን የኤሌክትሪክ ክፍያ እንድትፈፅም የሚያስችል የስምምነት ህግ ማፅደቋን አሜሪካ አስታውቃለች፡፡

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የኢራቅን ብሄራዊ ደህንነት የሚመለከቱ እና ለ120 ቀናት ይቆያሉ የተባሉ የህግ ማዕቀፎችን አፅድቀዋል፡፡

ሚኒስትሩ ከፈረሟቸው የህግ ማዕቀፎች ውስጥ የኢራቅ የብሄራዊ ደህንነት ዋና ጉዳይ የሆነው የሀገሪቱ ኤሌክትሪክ ሀይል ሲሆን አሜሪካ ኢራቅ ለኢራን የኤሌክትሪክ ክፍያ እንድትፈፅም ፈቃዷን ሰጥታለች፡፡

ይህ ስምምነትም ኢራን በክረምቱ ወራት የሚያጋጥማትን የሀይል መቆራረጥ ያስቀርላታል ነው የተባለው፡፡

እንደ አሜሪካ ባለስልጣናት ገለፃ ስምምነቱ በተለይም ኢራን የኤሌክትሪክ ሀይልን በተመለከተ በባግዳድ ላይ የምታሳድረውን አሉታዊ ተፅዕኖ ይቀንሳል፡፡

አሜሪካ ቀደም ሲል ኢራን ወደ ኢራቅ የምትልከውን የተፈጥሮ ጋዝ እንድታቋረጥ እና የምታመነጭው የኤሌክትሪክ ሀይል ገደብ እንዲኖረው አድርጋ መቆየቷን ኢንዲያ ቱዴይ ዘግቧል፡፡