የሀገር ውስጥ ዜና

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

By Tamrat Bishaw

July 22, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ የስራ ዘመን አምስተኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው በቆይታው የክልሉ መንግስት የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የገጠር መሬት አስተዳደር የእርሻ እና ሌሎች አዋጆችን ማጽደቅን ጨምሮ ለተያዘው የስራ ዘመን የክልሉ መንግስት ማስፈጸሚያ በጀት እና እቅድ ላይ ይመክራል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በጉባኤው የምክር ቤቱ አባላት፣ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል።