የሀገር ውስጥ ዜና

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

By Amare Asrat

July 22, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ።

 

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሀገሪቱ ውስጥ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት በተለይም ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች ባገኙት ገንዘብ 27 ሁለተኛና አዳሪ ትምህርት ቤቶችን አስገንብተዋል።

 

ትምህርት ቤቶቹ በርካታ ተማሪዎች መቀበል አንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን ትምህርት ቤቶቹም ደረጃቸውን የጠበቁ መሆኑን ኢዜአ በዘገባው አመላክቷል።

 

ትምህርት ቤቶቹ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በአማራ፣ በአዲስ አበባ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በጋምቤላ ክልሎች መገንባታቸውም ታውቋል።

 

የክብር ዶክተሬቱም ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በትምህርትና በሰብዓዊ ልማት ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክተሬቱ እንደተሰጣቸው ተገልጿል።