የሀገር ውስጥ ዜና

የትምህርት ሚኒስትሩ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞችን ጎበኙ

By Alemayehu Geremew

July 24, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ጎብኝተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)ና ሚኒስትር ዴኤታው ሳሙዔል ክፍሌ (ዶ/ር) ÷ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢና በ4 ኪሎ ሳይንስ ፋካሊቲ ተገኝተው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን አበረታተዋል።

በዩኒቨርሲቲው ያለውን የተማሪ አቀባበል ፣ የመኝታና የመመገቢያ ቦታዎችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በምልከታቸውም ተፈታኝ ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲሰሩ ሚኒስትሩ አበረታተዋል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።